Open Access Week

October 23 - 29, 2023 | Everywhere

የ2020 የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት የትኩረት አቅጣጫ “ግልጽነት ከአላማ ጋር፡- መዋቅራዊ እኩልነትንና አካታችነትን ለመገንባት ለተግባር እንነሳ” የሚል ይሆናል፡፡

በቀጣይ ዓመት ከጥቅምት 9 እስከ ጥቅምት 15 2013 .ም የሚከበረው የዓለምአቀፍ የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት የትኩረት አቅጣጫ፤ “ግልጽነት ከአላማ ጋር፡- መዋቅራዊ እኩልነትንና አካታችነትን ለመገንባት ለተግባር እንነሳ” የሚል መሆኑን የ2020 የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት አማካሪ ኮሚቴ በደስታ ያበሥራል፡፡

ግልጽነት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የእውቀት ማጋራት ሥርዓት ለመገንበት ዋና መሣሪያ ነው፡፡የምርምርና የትምህርት ሥርዓቱን እንደገና በማዋቀር በዋናነት በግልጽ ተደራሽ ማረግ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ሥርዓት ለመገንባት መሰረት ይጥላል፡፡ ነግር ግን አሁንም ግልጽነት ዋና እሴት በሆነባቸው ቦታዎች ሳይቀር መዋቅራዊ ዘረኝነት ፣አድሎነትና አግላይነት ቀጣይነት ባለው ሁነታ ይታያል፡፡እንደ ዓለምአቀፍ ማሕበረሰብ መገንዘብ ያለብን አሁን ያሉት ሥርዓቶችና ሁኔታዎች የተገነቡት በታሪካዊ እፍታሕዊነት ላይ መሆኑን መገንዘብና እኩሉነትን ለማምጣት መፍትሔ ማበጀት አስፈላጊ ነው፡፡

አሁን ያሉትን ሥርዓቶችና ሁኔታዎችን ለማን ተሰሩ ፤ማንን አላካተቱም ፤ በምንጠቀማቸው የድርጅት አሰራሮች እነማን ናቸው የተገለሉት እና የማን ፍላጎት ነው ቅድሚያ የተሰጠው የሚሉትን ጭብጦች አካተን መፈተሽ አለብን፡፡የእነዚህን መዋቅሮች መሰረት በድጋሚ በምናስተካክልበት ጊዜ ተጨባጭ ውጤቶች ለማሥመዝገብ ከንግግር አልፈን ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድና ተጠያቂነት ማስፈን ያስፈልጋል፡፡

2018 ..አ የተደረጉ ውይይቶችን መሰረት በማረግ (“ለግልጽ እውቀት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መሰረት እንጣል”) እንዲሁም በ2019 .. (“ግልጽነት ለማን? እኩልነት በግልጽ እውቀት“) ላይ በመመርኮዝ ፤ የ2020 (..) ቀጣዩ ሦስተኛው የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት የትኩረት አቅጣጫ የሚያመላክተው አንገብጋቢ የሆኑትን እኩልነትንና አካታችነትን ለማምጣት ተግባራዊ እርምጃ እንዲወሰድና ጉዳዩንም ወደ መሀል አምጥቶ ትኩረት እንዲሰጠው ማረግ ነው፡፡

የዓለምአቀፍ የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት በሚከበረብት ጊዜ ሰፊው ማሕበረሰብ ተቀናጅቶ በምርምር ላይ ግልጽ ተደራሽነትን ዋና ትግበራ በማረግና እና እኩልነትን የዚህ ሥራ አንኳር በማረግ ማረጋገጥ ያሥፈልጋል፡፡

የዚህ ዓመት(2020 ..) የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት ከጥቅምት 9 እስከ ጥቅምት 15 2013 .ም ይከበራል፡፡ነገር ግን አስተባባሪዎች የአከባቢያቸውን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ በተመቻቸው ጊዜ ሊያረጉት ይችላሉ፤እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫውንም ለአከባቢያቸው በሚስማማ መልኩ ሊያሻሽሉት ይችላሉ፡፡በተለይ በዚህ ዓመት በኮቪድ-19 ወረርሽኞች ምክንያት መስተጓጎሎች ሊገጥሙ እንደሚችሉ ስለምንገነዘብ ልክ እንደ አከባቢው ሁኔታ ማክበር ያስፈልጋል፡፡

የግልጽ ማሕበረሰብ በሙሉ በዚሕ ዓመት መሉውን ጊዜ ከሚገነቡ መሰረተ ልማቶቻችን ጀምሮ እስከ የምናስተባብራቸው የማሕበረሰባችን የውይይት መድረኮች ድረስ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ብዝሀነትን፣እኩልነትንና አሳታፊነትን ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡የዓለምአቀፍ የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት አዳዲስ ውይይቶችን ለማነሳሳት፤ በማሕበረሰቡ መሀከል እንዲሁም ከሌሎች ማሕበረሰቦች ጋር አብሮ ለመስራት ግንኙነት ለመፍጠር እና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የግልጽ እውቀት መሰረት

የመጣል ሥራን ለማቀላጠፍ ትልቅ ዕድል ነው፡፡ውይይቶቻችንና ተጋባሮቻችን ዐመቱን ሙሉ ሳያቋርጡ ሊቀጥሉ ይገባል፡፡

ስለዓለምአቀፍ የግልጽ ተደራሽነት ሳምንት የለበለጠ መረጃ ከፈለጉ ይህን ድረገጽ ይጎብኙ www.openaccessweek.org. የሳምንቱ አከባበር ይፋዊ የቲዊተር ሃሽታግ #OAWeek ነው፡፡

Views: 750

Comment

You need to be a member of Open Access Week to add comments!

Organized by:

in partnership with our
Advisory Committee

Twitter Feed

All content subject to a Creative Commons Attribution 4.0 License unless specified differently by poster.   Created by Nick Shockey.   Powered by

Badges  |  Report an Issue  |  Terms of Service